Monday, October 30, 2017

የዋልድባ ገዳም መፍረሱን በመቃማቸው ነው አሸባሪ ተብለው ለእስር የተዳረጉ


በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሁለት መነኮሳት መንግስት በአሸባሪነት ጠርጥሬአችኋለው ብሎ ያሰራቸው ናቸው። የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ሲሆኑ፤ አባ /እየሱስ /ማርያም እና አባ /ስላሴ /ሃይማኖት ይባላሉ። አለም በቃኝ ብሎ በገዳም መቀመጥም አይቻልም ማለት ነው። የዋልድባ ገዳም መፍረሱን በመቃማቸው ነው አሸባሪ ተብለው ለእስር የተዳረጉት። መነኮሳቱ 2004 ጀምሮ አቤቱታቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውንም ይናገራሉ። መነኮሳቱ በማእከላዊ ቆይታቸው ድብደባ ሌሎች ሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል። ክስ ተመስርቶባቸው ቂሊንጦ ከወረዱ በኋላም ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንዳልተለያቸው እንዲሁም ከሌሎች አብረዋቸው ከሚኖሩ እስረኞች ጋር አብረው እንዳይበሉ እና እንዳይጫወቱ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑንም ተናግረዋል። 

ችሎታቸውን ለመከታተል የምትፈልጉ ቀጣይ ቀጠሯቸው ህዳር 14 ነው። ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4 ወንጀል ችሎት።


#ምንጭ MahletFantahun

No comments:

Post a Comment