Monday, May 22, 2017

His Ph.D thesis is Plagiarized from Dr Mebratu Kiros


  • He didn't get his first degree from HTTC and His Ph.D thesis is Plagiarized from Dr Mebratu Kiros. UNISA have erased his thesis from its site after it knows his plagiarism so he is no more Dr.
ጥያቄ /ር  አባ /ማርያም
  • አባት ስም እና የትውልድ ዘመን መቀየር ??!! 
  • ከ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ??!!
  •  በከፍተኛ ትምህርትም ( ከዶክትሬት ዲግሪ) መመረቂያ (Plagiarized  issue)


(Prevouse Comment) 
በአውነት ለኤጲስቆፖስነት ምርጫ የሚደረገው ሩጫ የሚጠበቅ ስለነበረ የሚያስገርም አይደለም፡፡እነዚህ ሁሉ አባቶች በትክክል ቤተክርስትያናችንን ለማገልገልና በአደራ የተቀበሏቸውን የእግዚአብሔርን በጎች ለመጠበቅ ተዘጋጅተው ከሆነ መልካም ነው፡፡ነገርግን በብዙ መልኩ የሚያጠራጥሩ ነገሮች መኖራቸው አልቀረም፡፡ "/" አባ /ማርያምን በሚገባ አውቃቸዋለሁ፤የማታውቋቸው ካላችሁ ደግሞ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ-ስበከት ሆለታ ከተማ ላይ በመገኘት በገነት ኪዳነምህረትና በደ/ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የነበራቸውን የኋላ ታሪክ ማጣራት ትችላላችሁ፡፡ ግለሰቡ 1993 . በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ እንደነበር የሚታወቅ ነው፤ነገርግን የጀመሩትን ትምህርት ሳያጠናቅቁ ወደ ኖርዌይ ሄዱ ተባለና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሳይቀበሉ የሄዱ ሰውዬ "ዶክተር" ተብለው መጡ፤ ማስተርስ ዲግሪና .ኤች. ያለምንም ውጣ ውረድ ይሏል ይሄ ነው! ስንት ድራማ የሚሰራባት ሀገር ባለቤት በመሆናችን እንኮራለን!!! የሚመለከታቸው አባቶች በጥንቃቄ ቢያጤኑት ይበጃል፡፡ ሆለታ //ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የነበረውን ሰፊ ቦታ ለማን አሳልፈው እንደሰጡት እግዚአብሔር ያውቃል፤የቤተክርስትያኑ ገንዘብ በቀን ጅቦች ሙልጭ ተደርጎ ሲዘረፍ ዋና ተዋናዩ ማን እንደነበር ሄዶ ማጣራት ይቻላል፡፡ ለማንኛውም ምኑ ተወርቶ ምኑ ይተዋል፤እኔም የእሳቸውን ኃጢኣት ለማብዛትና በራሴ ላይ የበደል ዕዳ ለመከመር ሳይሆን እውነቱን እያወቅሁ ህሊናዬን ከሚቆረቁረኝ የማውቀውን ብተነፍስ ይሻላል በሚል ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ "…ዘይሁብ መርዓ ርቱዐ ለቤተክርስትያን…" እንደተባለው ለቤተክርስትያን ቅን መሪን መስጠት የሚችል አምላክ ለቤተክርስትያናችን የሚበጁና መንጋውን የሚጠብቁ እውነተኛ አባቶችን ይሰጠን ዘንድ አምላካዊ ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!!!

1 comment: