Sunday, March 12, 2017

በድንገት ተቀስቅሶ የዝቋላ ተራራን ደን ያቃጠለው እሣት በቁጥጥር ስር ዋለ


EBC መጋቢት 032009
በድንገት ተቀስቅሶ የዝቋላ ተራራን  ደን ያቃጠለው የእሣት አደጋ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገለፀ፡፡ የ3ሺህ ሜትር ከፍታ ያለው  በዚሁ የዝቋላ ተራራ ከዚህ በፊት ሙሉ ለሙሉ በደን የተሸፈነ እንደነበር ይነገራል፡፡
የአቡነ /መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኝበት ይኸው ገዳም ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን የአካባቢው ህብረተሰብ  ደኑን ለተለያዩ ግልጋሎቶች  እየተጠቀመበት በመምጣቱ  ተራራው እየተራቆተ መምጣቱም ተመልክቷል፡፡ አሁን ደግሞ የዝቋላ ተራራን ሸፍኖ የሚገኘው ደን ሳይታብ በተነሳው ድንገተኛ እሳት ሰፊው ቦታ የሚሸፍነው ደን መቃጠሉ ተገልጿል፡፡
ይሁንእንጂ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የኢትዮጵያ አየር ኃይል  ሰራዊት አባላት ፣የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የገዳሙ ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ  በቁጥጥር  ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡ስለደኑ የቃጠሎ መንስኤ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ደኑ ከቅርብ አመታት ወዲህ በተደጋጋሚ የመቃጠል አደጋ እያጋጠመው በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ደኑን መልሶ ለመተካት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል፡፡


No comments:

Post a Comment