Thursday, July 21, 2016

ስለ አባ ሚካኤል ገ/ማርያም የፅኑዋኑን ምዕመናን እንባ እና በሀዘን የተሰበረ ልብ ሂዱና አድምጡ




ከአላባ እና ከምባታ አካባቢ ምዕመናን የተሰማ የመጨረሻ ቃል….

 የጵጵስና ማዕረግ አስመራጭ ኮሚቴው ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀበለው ከባድ ሃላፊነት በመመልከት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸውን መነኮሳትና ቆሞሳት በመቀበል ባስቀመጠው መመዘኛ መሰረትማለት ምንኵስናቸውና ገዳማዊ ሕይወታቸው አጠራጣሪና በቂ ማስረጃ የሌላቸው፤  በትውልድ አገራቸው በሥርዓተ ተክሊል ያገቡና ጋብቻቸውን ያፈረሱ፤  ጋለሞታዎች፤  ባለትዳሮችን የሚያማግጡ፤  ከተለያዩ ሴቶች የወለዱ፤  በአብነቱም በዘመናዊውም ትምህርት  የተጭበረበረ ማስረጃ የያዙ፤  ከተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናት በምዝበራቸው የተባረሩ ጵጵስናውንም የዚኹ ሽፋን አድርገው ሀብት ለማድለብ የሚቋምጡ፤  በጠንቋይነትና አስጠንቋይነት፤ በመተተኛነት ለነፍስ መጥፋት ምክንያት የኾኑ፤  በእምነታቸው ጉልሕና ተጨባጭ ሕፀፅና ነቀፌታ ያለባቸው፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንም በኅቡእ የሚሠሩና ሽፋን የሚሰጡ፤  እጩዎችን በወንፊት ነፍቶ ብዙዎችን በመቁረጥ እዚህ ደረጃ ላይ 31 ያላቸውን በማስቀረቱ ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ ነገር ግን እኛ በደንብ የምናውቃቸው ለዓመታት ምዕመኑን ሲያስለቅሱ የነበሩ አባ ሚካኤል ገ/ማርያም በዚህ መስፈርት ተመዝነው እዚህ ደረጃ መድረሳቸው አግራሞትን ፈጥሮብናል፡፡


ከ31 እጩዎች ውስጥ የተገኙት አባ ሚካኤል ገ/ማርያም አሁንም በከንባታ እና በአላባ የሚገኙ ምዕመናን የጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴ እና ቅዱስ ሲኖዶስ  ያለፉበትን መንገድ ፤ ያለባቸውን ከባድ ነቀፌታ በማየት ለምዕመናን አንድነት የማይጠቅሙ ሰው መሆናቸውን ተገንዝቦ በመጀመሪያ ደረጃ ከተጠቆሙት መነኮሳት እና ቆሞሳት ውስጥ እንዴት እዚህ ደረጃ እንደደረሱ ጥልቅ ማጣራት ያደርግ ዘንድ  የልጅነት ምክራችንን እየገለፅን ፤ እኚ አባት ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ ለቤተክርስቲያኒቱ ለአዲስ ምዕመን በር በመክፈት ስርዓተ ጥምቀትን እንዲያገኝ ከማድረግ ይልቅ በቀድሞ ባሕሪያቸው ከተሀድሶያውያን ጋር በመሆን ለቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ፈተና እንደሚሆኑባት አበክረን መናገርና መግለጽ እንወዳለን፡፡ የቀድሞ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መልከፄዴቅን ባስተዳደሩት ሀገረ ስብከት ላይ አባ ሚካኤል ገ/ማርያም ጳጳስ ሆኖ መመልከት ለቤተክርስቲያናችን ፤ ለምዕመኗ ፤ ለአገልጋይ ካህናቶቿ በጠቅላላ የደረስንበትን የሃይማኖት የቁልቁለት መንገድን የሚያመላክት ነው፡፡

እሳቸው እንኳን ለጵጵስና ቀርቶ ለድቁና እንኳን የሚያበቃ ስነ ምግባር የሌላቸው ሰው መሆናቸውን ስራ አስኪያጅ ሆነው ካስተዳደሩበት አብያተ ክርስቲያናት መረጃ ይወሰድ !!! በእኛም ላይ መከራን አታውርዱብን ቤተ-ክርስቲያናችንም የመናፍቃን መሳቂያ እና መሳለቂያ ከመሆን ታደጉዋት እባካችሁን ኑና እውነታውን ከሕዝበ ክርስቲያኑ ስሙ!!! ኑና እውነታውን ለመናፍቃን ከሸጡት የዱራሜ የጥምቀት ቦታ ፤ 600 ዓመታት በላይ ታሪክ ካለው ከፈረሰችው እና በቅርቡ መናፍቃን አዳራሽ ሊሰሩበት ከሚያስቡበትት አምባሪቾ ማሪያም፤ ከሃላባ እመቤታችን፤ ከሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመናን እና ከካህናት
አባቶቻችን እባካችሁ የፅኑዋኑን ምዕመናን እንባ እና በሀዘን የተሰበረ ልብ ሂዱና አድምጡ



No comments:

Post a Comment