Friday, August 19, 2011

መዝሙሮቻችን ድሮና ዘንድሮ

እናስተውል.........
በፊት በፊት የመዝሙር ግጥሞች ሲፃፉ እግዚሐብሔር እንዲመራቸው በፆምና በፀሎት እግዚሐብሔርን መጠየቅ የነበረ ሲሆን አሁን አሁን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተብሎ የሚወጣው መዝሙር ግጥም ከመናፍቃን የመዝሙር ካሴት ግጥም ኮፒ እየተደረገ መቅረብ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በተጨማሪም ሆን ተብሎ ለቸብቸቦ የሰውን ስሜት እንዲገዛ ተደርጎ ከመፃፉም ባሻገር አንዳች ነገር ለመዝሙር ሰሚው ወንጌልን የማስተላለፍ ሚናው በሙሉ ጠፍቷል ፡፡ ለምሳሌ ለማሳያ ያህለል ዘርፌ ከበደ አወጣሁት ካለችው መዝሙር ሁለት ያህል ግጥሞች አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፃፍኩ ያለው ሲሆን በጊዜው እነዚህ ግጥሞች ከመናፍቃኑ ካሴት ምንም ለውጥ ሳይኖራቸው የተገለበጡ በመሆኑ የግጥሙ ባለቤት ግጥሜ ተሰርቆብኛል ሲል አቶ በጋሻው ደሳለኝን ፍርድ ቤት መክሰሱ የሚታወስ ቢሆንም በምን አይነት ሁኔታ የፍርድ ቤቱ ፋይል እንደተዘጋ ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡ 

አቶ በጋሻው ደሳለኝ የመናፍቃንን ካሴት እየቃረመ ለእኛ ማቅረቡን የለመደው የቀን ተቀን ስራው መሆኑን ለማወቅ ‹‹የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን›› የሚለውን መፅሀፍ ለመፃፍ የፓስተር መለሰ ወጉን የስብከት ካሴት ቁጥር 107 ገልብጦ የተጠቀመ ሲሆን ይህን ስራውን በዘርፌ ካሴት ላይም ደግሞት ለማየት በቅተናል፡፡ ለማስረጃ ያህል የሚቀጥለውን ካሴት ስቲከር ይመልከቱ 

ቀጣዩን. ...... Click Read More 

በዚህው ከቀጠልን ነገ ያሬዳዊ መዝሙር የሚለውን ቃል ላለመስማስ ረዥም ጊዜ የሚወስድብን አይሆንም፡፡ ግጥሙን ፤ የወንጌል መልዕክቱን ፤ ያሬዳዊ የዜማ ጣዕሙን ሁለቱን መዝሙሮች አይተው ፍርዱን ለመስጠት ለእርስዎ ትተናል፡፡


አላፋና ኦሜጋ...(ኪነ ጥበብ)
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሀዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ

          ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
          እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
          ፅድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
          ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ

ኣዝ----------------------------
ቅዱሳን እጆችህ በፊጥኝ ታስረው
እንደ በግ ተጎተትህ ብትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመፃደቅ
ኣዝ----------------------------
          በአውደህ ምኩናን ከጲላጦስ ዘንድ
          አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድህ
          ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
          ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
ኣዝ ----------------------------
ግርፋት ህመሙ አልበቃህ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
አምስቱ ችንካሮች ቅንዋት መስቀል
ወገኖችህ መጡ ስጋህን ለማቁሰል
----------------------------
          የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
          ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
          ምራቅን ተፉብህ ራስክን ሊጎዱ
          ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ኣዝ----------------------------



የሀብታሙ ሽብሩ መዝሙር
አይቀርም መንጋቱ ቀስ እያለ ይነጋል
ሲመሽ የሚያፅናን ውዳችን ይመጣል
የለም አንዳች ነገር ትጥቅን የሚያስፈታ
ዛሬም ሆነ ነገ ያሸንፋል ጌታ
...............................
እስከ ጊዜው ነው የሃማ ዜማ
የእውነቱ ዳኛ ፍርድ እስኪሰማ
ባለ ሚዛኑ ንጉስ ይመጣል
እመኑ ነገ ይገለበጣል
…………………………..
ሀዘን ቢገፋን ወደ ኤማሁስ
ይደርስልናል ሲመሽ ኢየሱስ
የአጥቢያ ኮከብ ነው ሌቱን የሚያነጋ
ጠላት ይመታል በደሙ አለንጋ
………………………………..
የወይን ግንዱ ቅርንጫፎች ነን
በጎኑ ቁስል የለመለምን
አይጠወልግም ወንጌል መዝሙሩ
የክርስቶስ ደም አለ ከስሩ
……………………….
ሃያሉ ስሙን ከተሸከምነው
ብንገደለም ትንሳኤአችን ነው
ብንቆጠርም ከሟቾች ተርታ

ይህስ ከየትኛው የመናፍቃን ካሴት የተገለበጠ ነው?…. ….. 


       
  ‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

2 comments:

  1. sele merejawe enamesegenalen....bezu neger enetebekalen

    ReplyDelete
  2. this indicates how they are fighting this holly church? does this a protestant or a christian song

    ReplyDelete