Tuesday, January 24, 2017

በዓለ ጥምቀት በዝዋይ ሐይቅ
(Reporter)
ዓመታዊው የጥምቀት በዓል ከተከበረባቸው ቦታዎች መካከል በዝዋይ ሐይቅ ውስጥ የሚገኙት ገዳማት ይጠቀሳሉ፡፡ ከአዲስ አበባ 161 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ዝዋይ (ባቱ) ከተማ ዳርቻ፣ ባለው ሐይቅ የሚገኙት አቡነ ተክለሃይማኖት፣ ቅዱስ ሚካኤል፣ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም፣ አርባዕቱ እንስሳትና ፀዴቻ አቡነ አብርሃም ገዳማት ጥር 10 እና 11 2009 .. በዓሉን አክብረዋል፡፡ ከአምስቱ ገዳማት አቡነ ተክለሃይማኖትና ደብረ ጽዮን ከደሴታቸው በመውጣት ሦስት ኪሎ ሜትር የሚሆነውን የሐይቁን ክፍል አቋርጠው ምድር ላይ በማክበር ብቸኛ ያደርጋቸዋል፡፡ የተቀሩት ሦስቱ ደግሞ ከሐይቁ ዳር በጣም የራቁ በመሆናቸው ከቤተ መቅደሳቸው በመውጣት በግቢያቸው የሐይቁ ጠርዝ ላይ ድንኳን በመጣል እዚያው አክብረዋል፡፡ (ፎቶ በታምራት ጌታቸው)

Thursday, July 21, 2016

ስለ አባ ሚካኤል ገ/ማርያም የፅኑዋኑን ምዕመናን እንባ እና በሀዘን የተሰበረ ልብ ሂዱና አድምጡ
ከአላባ እና ከምባታ አካባቢ ምዕመናን የተሰማ የመጨረሻ ቃል….

 የጵጵስና ማዕረግ አስመራጭ ኮሚቴው ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀበለው ከባድ ሃላፊነት በመመልከት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸውን መነኮሳትና ቆሞሳት በመቀበል ባስቀመጠው መመዘኛ መሰረትማለት ምንኵስናቸውና ገዳማዊ ሕይወታቸው አጠራጣሪና በቂ ማስረጃ የሌላቸው፤  በትውልድ አገራቸው በሥርዓተ ተክሊል ያገቡና ጋብቻቸውን ያፈረሱ፤  ጋለሞታዎች፤  ባለትዳሮችን የሚያማግጡ፤  ከተለያዩ ሴቶች የወለዱ፤  በአብነቱም በዘመናዊውም ትምህርት  የተጭበረበረ ማስረጃ የያዙ፤  ከተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናት በምዝበራቸው የተባረሩ ጵጵስናውንም የዚኹ ሽፋን አድርገው ሀብት ለማድለብ የሚቋምጡ፤  በጠንቋይነትና አስጠንቋይነት፤ በመተተኛነት ለነፍስ መጥፋት ምክንያት የኾኑ፤  በእምነታቸው ጉልሕና ተጨባጭ ሕፀፅና ነቀፌታ ያለባቸው፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንም በኅቡእ የሚሠሩና ሽፋን የሚሰጡ፤  እጩዎችን በወንፊት ነፍቶ ብዙዎችን በመቁረጥ እዚህ ደረጃ ላይ 31 ያላቸውን በማስቀረቱ ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ ነገር ግን እኛ በደንብ የምናውቃቸው ለዓመታት ምዕመኑን ሲያስለቅሱ የነበሩ አባ ሚካኤል ገ/ማርያም በዚህ መስፈርት ተመዝነው እዚህ ደረጃ መድረሳቸው አግራሞትን ፈጥሮብናል፡፡

Sunday, July 17, 2016

አባ ሚካኤል ገ/ማሪያም ፡ እንኳን ለጵጵስና ላሉበት ምንኩስና የሚያበቃ ሥነ-ምግባርና የመምራት አቅም የላቸውም


ቀን፡-  08/11/08 .
 ለኢ/////////ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ ቆሞስ መላከ ጽዮን አባ ሚካኤል /ማሪያምን ይመለከታል
በስም ተጠቃሹ አባት የከምባታ ጠምባሮና ሀላባ /ስብከት /ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት ለጵጵስና ማዕረግ መታጨታቸውን በመገናኛ ብዙሓን ተገልፆ ሰምተናል። ዳሩ ግን እኒህ አባት እንኳን ለጵጵስና ላሉበት ምንኩስና የሚያበቃ ሥነ-ምግባርና የመምራት አቅም ያላቸው አባት ሳይሆኑ ለምዕመናን መሰናከያ ከመሆናቸውም ባሻገር የቤተክርስቲያንን ህልውና ደፍረው የሚያስደፍሩ ናቸው። ለዚህም መገለጫ ከሚሆኑት ጥቂቶቹን ብንጠቅስ፦
1) ኮረዳዎችን ከዱራሜ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመውሰድ ቤት ተከራይተው በቅምጥነት የሚያኖሩና ለሥራ ወደሄዱበት ሁሉ ይዘው በመዘዋወራቸው አገር ጉድ ያላቸው ናቸው።

2)የሥነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸውን መንገደኛ የሆኑ መነኮሳትን በየአድባራቱ እያሰማሩ ቤተመቅደሶችን ያስመዘበሩ ናቸው። ለአብነት ብንጠቅስ፦